የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል 142 የታገዱ ድርጅቶች ግንቦት 02፣2015 (ገቢዎች ሚኒስቴር)
ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚዲያ)
በ2017 በጀት ዓመት በእቅድ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካት በ13ቱም የፌዴራል የገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ጽ/ቤቶች የተመደቡ ቡድኖች ከመስከረም 13- 23/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ በየቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ድጋፍ እና ክትትል ተደርጓል፡፡
የድጋፍ እና ክትትል ቡድኖቹ በተቀመጡ 6 ዋና ዋና ድጋፍ የሚደረግባቸው መስፈርቶች በ13 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጥንካሬና ድክመቶች፣ ቁልፍ ችግሮችና ከዋና መ/ቤት የሚጠበቁ ድጋፎች መረጃ ሰብስበዋል፡፡
ከዕቅድ ዝግጅትና ፈጻሚን ከማዘጋጀት አንፃር፣ ምቹ የሆነ የስራ ቦታና የግብዓት አቅርቦት ሁኔታ፣ የተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጥ፣ የገቢ ፊዚካል ሥራዎች አፈጻጸምና ያሉባቸው ተግዳሮቶች እንዲሁም ሌሎችም መስፈርቶች መመዘኛዎች ነበሩ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ድጋፍና ክትትል ሪፓርት መሰረትም በዛሬው እለት ውይይት የተካሄደ ሲሆን በሪፖርቱ የሚታዩ ክፍተቶችን ለይቶ በፍጥነት ወደስራ መገባት እንዳለበት ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡ በተለይም ቅዳሜ ሙሉ ቀን መስራትና ከስራ ሰዓት ውጪ መሰራቱ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክብርት ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የሰሜን ምእራብ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በስም የተዘረዘሩት 142 ግብር ከፋዮች ለሶስት እና ከሶስት ዓመት በላይ ግብር ያላሳወቁ ታክስ ከፋዮች የሒሳብ መመዝገቢያ መሳሪያ፣ ያሳተሙት ደረሰኝ፣ በተለያየ የታክስ አካውንቶች እዳ ያለባቸው በመሆኑ ያሳተሟቸው እና ሲገለገሉባቸው የነበሩ የተለያዩ ደረሰኞች ለታክስ አላማ የማያገለግሉ መሆናቸውን እነዚህ ደረሰኞችን በማናቸውም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አገልግሎት ላይ ውለው የተገኙ ከሆነ ህጋዊነት የሌላቸው እንደሆነ አሳውቆናል በመሆኑም ግብር ከፋዮቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ጥንቃቄ እንድታደርጉ መልእክታችንን እናስተላልፋለን!